About Us(ስለእኛ)

ስለ ሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት

 

የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አባላትን ጨምሮ በመላው ዓለም ከ 19 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ዋና የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ናት። የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና ኢየሱስ በቅርቡ እንደሚመጣ ለሰዎች ለማሳወቅ ትፈልጋለች።

አድቬንቲስቶች የሦስት አካላት ሥላሴ ማለትም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እንደሆኑ ያምናሉ ።እነሱም፥ ወልድ ኢየሱስ በቤተልሔም ህፃን ሆኖ ወደ ምድር በመምጣት እንደ አባቱ ፈቃድ ያለሀጢአት በመኖሩ፣ ደህንነት የሚቻል አድርገዋል።  ኢየሱስ ለዓለም ህዝብ ኃጢያት  መስዋዕት ሆኖ በሦስተኛው ቀን ከሞት በመነሳቱ ድል ለሁሉም ተደርጏል።

ከትንሣኤው በኋላ ወደ ሰማይ ሲመለስ፣ ኢየሱስ አፅናኝና አማካሪ ሆኖ  እንዲያገለግል መንፈስ ቅዱስን ተወልን፣ የደህንነት ዕቅዱን ለማጠናቀቅና ህዝቦቹን ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመዉሰድ ሁለተኛ እንደሚመጣም ቃል ገባ። የአድቬንቲስት ተከታዮች ያንን ቀን  በመጠባበቅ ከሚገኙት አማኞች መካከል ናቸው።

አድቬንቲስቶች እግዚአብሔር ለሰዎች ህይወት ጥራት ግድ እንዳለዉና ሁሉም ነገር፤ የአኗኗራችን ሁኔታ፣ አነጋገራችን፣ የርስ በርስ አቀራረባችን ሁኔታና ለአከባቢያችን የምናደርገዉ ጥንቃቄ የእቅዱ ክፍል መሆኑን ያምናሉ። ቤተ-ሰባችን፣ ልጆቻችን፣ ሥራችን፣ ችሎታችን፣ ገንዘባችንና ጊዜአችን ሁሉ ለሱ አስፈላጊ ናቸዉ።

FIND OUT MORE